top of page

 

እንኳን ደህና መጡ 

 

እኔ የ ባህራን ነኝ፥ ስራዎቼን እዚህ ያገኛሉ።

   አጫጭር ልቦለዶች

 

ኡበር

 አጭር ልቦለድ

                          በ የ ባህራን

 

ትራፊኩ ያለወትሮው ይትርመሰመሳል። 'ኡበር' የተሰኘውን ይህን የታክሲ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ ወዲህ የኦስሎ ጎዳናዎች እንደዚህ ስራ በዝቶባቸው አይቼ አላውቅም። የእግረኛውም ቁጥር ቢሆን የትየለሌ ነው። ሃገርህን ልቀቅ የተባለ ይመስል ካንዱ የመንገድ ዳርቻ ወደሌላኛው የተሰመሩለትን ነጠብጣቦች ተከትሎ ይተማል።

 

"ምን ሊሆን ይችላል" ራሴን ጠየቅኩ። ላፍታ ከፊትለፊቴ ካለው መንገድ አይኔን ነቅዬ ካጠገቤ ወንበር ላይ የተቀመጠውን ሳምሶናይት እየተመለከትኩ። ከሰከንዶች በፊት ነበር አንድ ከትከሻው ሰፋ ሰፋ ያለ ራስ ቅሉ ላይ ያሉና በሽሽት ላይ የሚመስሉ ቅንጥብጣቢ ጠጉሮቹን ወደ ላይ ያጎፈረ ፂሙን እንደ ጳጳስ ያንዠረገገ ወጠምሻ ምንነቱን ያላወቅኩት ሳምሶናይት አስታቅፎኝ እብስ ያለው።

 

እኔ በመሰረቱ ይህንን ስራ ስጀምር ሰው እንጂ ቦርሳ አመላልሳለው ብዬ አልነበረም። ጎረምሳው ባደረገልኝ ጥሪ መሰረት ከአስፋልት ዳር ስጠብቀው ከተፍ አለ። አልዘገየም። 

 

"ሃሎ" አለኝ በጎርናና ድምፁ የመኪናዬን የፊት ለፊት በር ከፍቶ።
"ሃሎ" አልኩ መልሼ። ሃሎ አለማቀፋዊ ቋንቋ ነው ብዬ ስላመንኩና በምንኛ እንደሚያወራኝ እስካውቅ ሌላ ቃል አልተነፈስኩም።

 

አሁን አሁን የኖርዌይ ዋና ከተማ የሆነችው ይቺህ ትንሽ መዲና ....

 

የቅርብ ጊዜ የግጥም ስራዎች 
 

ሰላም ምን ያደርጋል?

 

ሰላም ምን ሊፈይድ ሰላም ምን ያደርጋል?
ወኔን አሽመድምዶ ጡንቻን ያሟሽሻል
ጀግንነትን ሰርቆ በቁም አንበርክኮ በዳዴ ያስኬዳል

ሆ ... በል ያገሬ ሰው ነጋሪት ይነፋ
የሰው ነብስ እንገብር የለማውም ይጥፋ
በውሃ ቀጠነ በቆዳዬ ጠቦኝ ሰበብ እንስራና 
እንፎክር... እንጨፍር... እንሂድ ከጎዳና

 
                   ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ....

ባንዲራው

 

ይሆን ካቅላማቱ 
ወዘና ውበቱ
አልያ ከቁጭቱ
ዙርያ ዝምዝማቱ
ነው ጠረን መዐዛው ከስር ሚፈነቅል
ወይስ ወግ ተሆነ ከዘር ዘር የሚዘል
ሲያዩት መንሰቅሰቅ መታቀፍ መንጠልጠል

ማስታወቂያ
 
 
ድህረ ገጹን እና የ ባህራንን የተመለከቱ ወሬዎች
 

'ኡበር' የመጀመሪያ አጭር ልቦለድ ይፋ ሆነ::

ጥር 29 2008 

 

የባህራን ከግጥም ስራዎች ባሻገር አጭር ልቦለድ ይዞ በጥበብ ማዕድ ከተፍ አለ። ልቦለዱ 'ኡበር' የተሰኘና በእውነተኛ የህይወት ገጠመኝ ላይ ተመርኩዞ የተጻፈ ነው። 

 

የ ባህራን ድህረ ገጽ ይፋ ሆነ

ጥር 29 2008

 

የስነ ጽሁፍ ስራዎቹን ለጥበብ አፍቃሪያን ያቀርብ ዘንድ በዕለተ ቅዳሜ ጥር 28 2008 የ ባህራን ድህረ ገጽ ይፋ ሆነ። ይህ ድህረ ገጽ በፌስ ቡክ ብቻ ታጥሮ የነበረውን የባህራን የስነ ጽሁፍ ስራዎች ተደራሽነት በማስፋት ስራዎቹ ለአንባቢያን እንዲበቁ እንዲሁም ግብረ መልሶች ለ የ ባህራን እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

 

 

ምስል እና ድምጽ

ሌሎች የግጥም ስራዎች
bottom of page