top of page
ድህነት አይጥፋ
 
ያለው በሌለው ላይ ግፍ ሰሪ ከሆነ፣
ድፍን በሞላበት የኔ ቢጤ ድሃው ቁራሽ ከለመነ፣
ንዋይ ኪስ ሲሞላ ራስ ከሆነ ወና፣
ፍቅርን አንበርክኮ ሊገዛ ነውና፣
ያብሮነት ትውፊቱ ጉርሻም እንዳይጠፋ፣
ለናሙናም ቢሆን ድህነት አይጥፋ።
 
የ ባህራን
ጥር 26, 2008
bottom of page