top of page

 

ባንዲራው

 

ይሆን ካቅላማቱ 
ወዘና ውበቱ
አልያ ከቁጭቱ
ዙርያ ዝምዝማቱ
ነው ጠረን መዐዛው ከስር ሚፈነቅል
ወይስ ወግ ተሆነ ከዘር ዘር የሚዘል
ሲያዩት መንሰቅሰቁ መታቀፍ መነጠልጠል

 

እኔ እስከገባኝ ግን
የሰንደቅ ትርጉሙ

የባንዲራ ስሙ

ከቀለም ይደምቃል
ከጠረንም ይልቅ ከመዐዛም ይልቅ ወደ ውስ ይዘልቃል


እኔን እስከገባኝ

ይሄ ነው ትርጉሙ 
ጊዜ የማይሽረው ከትውልድ ትውልድ የሚወራረሰው ምንነት የስሙ
ብትገልጠው የማያልቅ በድሜ የጠገበ ትውልድ የከተበው
ጊዜ ማያልፍበት ያገርህ ኢቶዮጵያ የህይወት ታሪክ ነው

 

የ ባህራን 
ጥር 30 2008

bottom of page