እማ!
ካንቺ ከተዘራው ካንቺ ከተገኝው ከዚያች ዐጥቢያ አንስቶ:
በልግዋም እንዳለ ድምፅ እንደሌለው ሰው ልሳኔ ተዘግቶ:
ከቶ ያልነገርኩሽ ልነግርሽ የምሻው አንድ ምስጢር አለኝ:
ላመታት ተረግዞ በውስጤ የኖረ አልወጣልህ ያለኝ::
ደከመኝ ሰለቸኝ በቅቶኛል ማታውቂ:
ከዐለት የፀናሽ እንደ እስራኤል ሳምሶን ጠንካራ ነሽ አንቺ::
ዐለም ወረተኛ ፊትዋን አዙራብሽ መከራ ቢበዛ:
መሸነፍ አታውቂም እጅ መስጠት የለም እንዲሁ እንደዋዛ:
ሰው እንዳሸን በዝቶ ካለበት ከተማ:
ወገን አልባ ሁነሽ ስቃይሽ ቢጠና:ችግርን ተካፋይ ብታጪም ሁነኛ:
አንቺ ግን:
«ያለሰው አይኖርም» ብለሽ እየመከርሽ አሳድገሽናል:
ማክበር-የመከበር መውደድ-የመወደድ ዋጋ እንደሆኑ አስተምረሽናል::
ራስ ወዳዶች በዝተው በሞሉት ከተማ:
መሽቀርቀር ሳያምርሽ ሁነሽ ራስ አልባ:
ህይወትሽን ሙሉ ካብራክሽ ለወጣን ለኛ ለልጆችሽ ሰውተሽ ስትኖሪ:
አንዲት ቅዕበት እንክዋ በፈተና ታጠፈሽ ወድቀሽ ሳትቀሪ:
አቀበቱን ወጥተሽ ቁልቁለቱን ወርደሽ ላብሽን አንጠፍጠፈሽ ባኖርሽው መሰረት:
ይሀው እኛ ዛሬ ሰውነትን ወርሰን ጥንካሬን ለብሰን መሰረትን ህይወት::
ታዲያ ለሰጠሽን ተመን ለማይገልጠው ዋጋ አልባ በረከት
ቃላት አጥቼለት:እስካሁን ሳልነግርሽ ከልቤ አምቄ ደብቄሽ ያኖርኩት: አንድ ምስጢር አለኝ ቅድም ብዬሻለሁ:
እሱም:
እጅጉን አድርጌ:
እጅጉን አድርጌ: በጣም ወድሻለሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ታደለ ወርቁ (የ ባህራን)
መታሰቢያነቱ፥ ለእናቴ
17 ጥር 2008
